የአንገት መታጠፍ 'ቴክ ኔክ' እንዴት ይከሰታል?

By Sahle relation

የአንገት መታጠፍ 'ቴክ ኔክ' እንዴት ይከሰታል?

የዘመኑ አሳሳቢ በሽታ የሆነው የአንገት መታጠፍ 'ቴክ ኔክ' እንዴት ይከሰታል?

በዚህ ሰዓት ስልክዎን ወይም ኮምፒውተርዎን እያዩ ነው? እስቲ ለአፍታ ያቁሙ እና አቀማመጥዎን ይገምግሙ፤ ስልክዎን እና ኮምፒተርዎን የሚመለከቱት አቀርቅረው ነው? መልስዎ አዎ ከሆነ አንገትዎ ላይ ከባድ ሸክም ጭነዋል።

ማዮ ክሊኒክ ላይ በወጣ ጥናት መሰረት በርካታ ሰዎች በየቀኑ በአማካይ 3 ሰዓት ከ15 ደቂቃ ስልካቸው ላይ የሚያሳልፉ ሲሆን፣ በቀን ውስጥ ቢያንስ ለ58 ጊዜ ስልኮቻቸውን ይመለከታሉ።

በአሜሪካ ግማሽ ያህሉ ነዋሪዎች በየቀኑ በአማካይ ከ4 እስከ 5 ሰዓት ከተንቀሳቃሽ ስልካቸው ጋር እንደሚያሳልፉ ተገልጿል።

አንዳንድ ሰዎች ደግሞ በሥራ ምክንያት በቀን ለ8 ሰዓታት ያክል ከኮምፒውተር ጋር የሚያሳልፉ ሲሆን፣ ከሥራ በኋላ ደግሞ ቢያንስ በቤታቸው ከ2 እስከ 4 ሰዓታት ከኮምፒውተር ወይም ከስልካቸው ጋር ሊያሳልፉ ይችላሉ። 

ችግሩ ታዲያ ኮምፒውተር እና ስልክ በመጠቀም የሚያሳልፉት ጊዜ በአንገታቸው እና በሰውነታቸው ላይ ከፍተኛ ጫና የሚያሳድር ብሎም ለአንገት መታጠፍ እና የጀርባ ሕመም የሚዳርጋቸው መሆኑ ነው።

ተንቀሳቃሽ ስልክ ወይም ታብሌት ለመመልከት በ45 ዲግሪ ጭንቅላታችንን ወደፊት ስናዘነብል የአንገት መጣመም 'ቴክ ኔክ' ወይም 'ቴክስት ኔክ' በመባል የሚታወቀው የአንገት ሕመም የመከሰት ዕድሉ ከፍተኛ እንደሆነ ነው በጥናቱ ተመላክቷል።

በዚህ ሁኔታ አንገታችንን አዘንብለን ስንሠራ በአንገታችን፣ በትከሻችን እና በጀርባችን ላይ የሚደርሰውን ጫና ለማነጻጸር አንድ ጋሎን (3.8 ሊትር) ፈሳሽ አንገታችን ላይ አስረን ማየቱ በቂ ነው ይላል ጥናቱ።

ይህ ማለት ከጭንቅላታችን ክብደት በተጨማሪ ወደ አራት ኪሎ ግራም ተጨማሪ ክብደት ለተጠቀሰው ጊዜ ያክል በአንገታችን ተሸክመን መቆየት እንደ ማለት ነው፡፡

ሙሉውን ለማንበብ በአስተያየት መስጫው ላይ ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ

 ምንጭ፡-ebc

Search articles

Recent articles

    Loading...