የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የካንሰር ህክምና ማዕከል አስመረቀ

By Sahle relation

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የካንሰር ህክምና ማዕከል አስመረቀ

ሐምሌ 16/2017 ዓ.ም

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የካንሰር ህክምና ማዕከል አስመረቀ፡፡

በአሁኑ ሰዓት በሃገራችን እየተስፋፋ ያለው የካንሰር ህመም በእጅጉ አሳሳቢ ጉዳይ በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፣ ሆስፒታላችን በቅርብ ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ የካንሰር (oncology) ቀዶ ህክምና ማከናወኑ መግለፃችን ይታወሳል፣ ካሁን በፊት ማህበረሰባችን የካንሰር ህክምና ለማግኘት ሲቸገር የቆየ ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት ግን ሆስፒታሉ ተጨማሪ ግብዓት በማመቻቸት የካንሰር ምርመራ እና ህክምና አገልግሎት ይሰጣል፡፡ በዛሬው እለትም የሆስፒታሉ የቦርድ አባላት፣የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ አመራሮች፣ የዞን ጤና መምሪያ ሃላፊዎች እና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት የካንሰር ህክምና ማዕከሉ በይፋ ተመረቀ፡፡

ይህ የህክምና አገልግሎት የብዙ ማህበረሰብ የጤና ችግርን የሚቀርፍ፣ አላስፈላጊ ወጪ እና እንግልትን የሚያስቀር መሆኑንም ተገልጾአል፡፡

Search articles

Recent articles

    Loading...