የወባ በሽታ ምንድነው?
By Sahle relation
የወባ በሽታ ምንድነው?
ወባ በፕላስሞዲየም ጥገኛ ተውሳኮች የሚመጣ አጣዳፊ የትኩሳት በሽታ ነው
የበሽታው ምልክቶች፡-
ከፍተኛ ትኩሳት፣ላብ፣ማንዘፍዘፍና ብርድ ብርድ የማለት ስሜት፣ራስ ምታት፣የጡንቻ መጓጎል፣የድካም ስሜት፣ማቅለሽለሽ፣ማስመለስ እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡
መተላለፊያ መንገዶች፡-
የወባ ተህዋሲያን፣ፕላስሞዲያ ተብለው የሚጠሩ ባለ አንድ ሴል ፍጥረታት ሲሆኑ ወደ ሰው ደም ውስጥ የሚገቡት አኖፊልስ በምትባለው ሴት ትንኝ ንክሻ አማካኝነት ነው፡፡ተህዋሲያኑ የግለሰቡ ጉበት ሴሎች ውስጥ በመግባት ይራባሉ፡፡በጉበት ውስጥ ያሉት ሴሎች ሲፈነዱ ተህዋሲያኑ ይወጡና የግለሰቡን ቀይ የደም ሴሌች ይወርራሉ፡፡ከዚያም ተህዋሲያኑ በቀይ የደም ሴሎች ውስጥ መባዛታቸውን ይቀጥላሉ፡፤የወባ ተህዋሲያን ቀይ የደም ሴሎችን ይወሩና ሌሎቹ እንዲፈነዱ ያደርጋሉ፡፡ቀይ የደም ሴሎቹ በሚፈነዱበት ወቅት ተህዋሲያኑ ይወጡና ሌሎች ቀይ የደም ሴሎችን ይወራሉ፡፤በቀይ የደም ሴሎች ውስጥ የሚካሄደው ይህ ዑደት ይቀጥላል፡፡ ቀይ የደም ሴሎች በፈነዱ ቁጥር በበሽታው የተያዘው ሰው የወባ በሽታ ምልክቶች ይታዩበታል፡፡
የወባ በሽታ መከላከያ መንገዶች፡-
የወባ ወረርሽኝ በተደጋጋሚ በሚከሰትበት አካባቢ ለሚኖር ማህበረሰብ
በፀረ ትንኝ ኬሚካል አብሮ የተሸመነ አጎበር መጠቀም
አጎበሩ የተባይ ማጥፊያ የተረጨበትና ምንም አይነት ቀዳዳ የሌለው ከዚያም በፍራሽ ዙርያ መጠቅጠቅ አለበት፡፡
የወባ ትንኝ በብዛት ከሚገኝበት ጥሻ የሆነ አካባቢ እና ለትንኝ መራቢያነት አመቺ የሆኑ የታቆሩ ውሃዎች ካሉበት ቦታ መራቅ ወይም የታቆረው ውኀ ማትፋት፡፡
በወባ የተያዘው ሰው በፍጥነት የህክምና እርዳታ እንዲያገኝ ጥረት ማድረግ
የወባ ወረርሽኝ ህክምና
በወባ በሽታ የተያዘን ሰው በአፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ህክምና ማድረግ ይጠበቅበታል፤አለበለዚያ በቸልተኝነት የወባ በሽታ እስከ ሞት ሊያደርስ ስለሚችል ማህበረሰቡ