ወሳኝ ስኬት በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

By Sahle relation

ወሳኝ ስኬት በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

የምስራች ለህክምና አገልግሎት ፈላጊ ማህበረሰባችን በሙሉ ወሳኝ ስኬት በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

‎በሆስፒታላችን ለመጀመሪያ ጊዜ የሴቶች የመራቢያ አካላት ካንሰር (Gynecologic oncology) ቀዶ ጥገና ማከናዎን ተጀመረ።

‎ከሴቶች የእንቁላል ማምረቻ እጢ የሚነሳ (Ovarian cancer) እና ከማህፀን የውስጠኛው ግድግዳ የሚነሳ ካንሰር (endometrial cancer) ቀዶ ጥገና በተሳካ ሁኔታ ለመጀመርያ ጊዜ ስናከናውን ዛሬ ለሆስፒታላችን ታሪካዊ ቀን ነው። ይህም በተቋማችን ውስጥ ከሴቶች የመራቢያ አካላት የሚነሱ የተለያዩ የካንሰር በሽታዎችን በመዋጋት ረገድ ትልቅ እድገት እና የሚያኮራ እርምጃ ነው።

‎ከዚህ በተጨማሪም ለካንሰር ታማሚዎች ህክምና አገልግሎት ወሳኝ ሚና የሚጫወተውን የኬሞቴራፒ አገልግሎትን ለማስጀመር የተለየ ዝግጅት በማድረግ የኦንኮሎጂ የህክምና አገልግሎት ክፍል መስርተናል።

‎የዚህን አዲስ አገልግሎት ተጠቃሚ ለምትሆኑ ታካሚዎች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ ።

‎የእናንተ ጥንካሬ እኛን የበለጠ ያነሳሳናል፣ ያበረታናልም።ሆስፒታላችን በዚህ ረገድ የሚሰጠውን አገልግሎት የበለጠ ለማስፋፋት እና በእንደዚህ አይነቱ ካንሰር ለሚሰቃዩ ወገኖቻችን ይህን የህይዎት አድን ህክምና በአቅራቢያቸው ለመስጠት በቁርጠኝነት ይሰራል።

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

Search articles

Recent articles

    Loading...