የከንፈርና የላንቃ መሰንጠቅ ህመም

By Sahle relation

የከንፈርና የላንቃ መሰንጠቅ ህመም

የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ እና የሃረር ፕሮጀክት ኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅት ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በጋራ በመሆን ለ6 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የከንፈርና የላንቃ መሰንጠቅ ህመም ያለባቸውን የማህበረሰብ ክፍሎች የነፃ ህክምና ዘመቻ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እንደሚሰጥ ተገለፀ፡፡

አገልግሎቱን የሚጀምረው ነገ ማለትም ህዳር 23/03/2015 ዓ.ም ለተከታታይ 6 ቀናት የሚቆይ ይሆናል፡፡ ይህንኑ የህክምና አገልግሎት የሚሰጣቸው የስልጤ ዞን፣ጉራጌ ዞን ፣ሃድያ ዞን፣ ከንባታ ጠንባሮ ዞን እና የም ልዩ ወረዳ ላሉ ማህበረሰብ ሲሆኑ ካሁን በፊት የተመዘገቡና አዳዲስ ማለትም የከንፈር ከ 4 ወር እና ከዚያ በላይ ያሉ ህፃናት እና አዋቂዎች ይሆናሉ፡፡ እንደዚሁ ደግሞ የላንቃ መሰንጠቅ ችግር ላለባቸው ከ 1 አመትና ከዚያ በላይ ያሉ ህፃናትና አዋቂዎች አገልግሎቱን ማግኘት የሚችሉ መሆኑን ሆስፒታሉ ይገልፃል፡፡

Search articles

Recent articles

    Loading...