‹‹የሲቲ ስካን ምርመራ›› ምንነት እና ጥቅሞች
By Sahle relation

ሲቲ ስካን (CT- scan) በጥራት እና በፍጥነት በመስራት የተዋጣለት ማሽን ነው፡፡
ሲቲ ስካን በሰውነታችን ውስጥ በርካታ ጥቅሞች ያሉት ሲሆን ከነሱም መካከል የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው
1. በአደጋ ጊዜ የተከሰተ የደም ስር እና አጥንት ጉዳት ካለ መኖሩን እና መጠኑን ለማወቅ ይጠቅመናል።
2. የተለያዩ በሽታዎችን ለመመርመር እና ያሉበትን ደረጃ ለማወቅ ያገለግላል። ለምሳሌ በሰውነታችን ውስጥ የሚወጡ እጢዎች እና ካንሰር እባጮችን ለማየት ፣ ኢንፌክሽን ካለ ለማየት፣ እና የሳንባ ጤና እክሎችን ለማወቅ ያስችለናል።
ለምርመራ የተለያዩ ናሙናዎችን ከሰውነታችን በትክክል ለመውሰድ ይጠቅመናል፡፡
3. የደም መርጋት ወይም መፍሰስ እንዲሁም የልብ ጤና ችግሮች ካሉ ለማየት ይጠቅመናል።
በተጨማሪም ህክምና ላይ ላለ ሰው የህክምና ለውጡን ለማወቅ እና ክትትል ለማድረግ እንጠቀመዋለን ።
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለማህበረሰቡ ከሚሰጣቸው ዘርፈ ብዙ የህክምና አገልግሎቶች ውስጥ የራዲዮሎጂ ምርመራ ክፍል አንዱ ነው፡፡
በራዲዮሎጂ ምርመራ ክፍል ውስጥ የሚሰጡ አገልግሎቶች፡-
የአልትራሳውንድ ምርመራ (ultrasound)
ራጅ (digital x-ray) ምርመራ
የሲቲ ስካን ምርመራ (CT-SCAN) የመሳሰሉት አገልግሎቶችን በራዲዮሎጂስት ሃኪም እና በራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂስት ባለሙያዎች አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡
