ለግቢ ጥበቃ ሰራተኞች ለ2 ቀናት ሲሰጥ የነበረው የእውቀት፣የክህሎትእና የአመለካከት ለውጥ ማምጣት የሚያስችል ስልጠና በስኬት አጠናቀቀ፡፡

By Sahle relation

ለግቢ ጥበቃ ሰራተኞች ለ2 ቀናት ሲሰጥ የነበረው የእውቀት፣የክህሎትእና የአመለካከት ለውጥ ማምጣት የሚያስችል ስልጠና በስኬት አጠናቀቀ፡፡

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላዝድ ሆስፒታል ለግቢ ጥበቃ ሰራተኞች ለ2 ቀናት ሲሰጥ የነበረው የእውቀት፣የክህሎትእና የአመለካከት ለውጥ ማምጣት የሚያስችል ስልጠና በስኬት አጠናቀቀ፡፡

የስልጠናው ዋና ዓላማ በተቋሙ ውስጥ ለሚሰሩ የጥበቃ ሰራተኞች በተሰማሩበት የስራ መስክ ላይ በትኩረት እና በትጋት ሃላፊነታቸውን በመወጣት መስራት እንዲችሉ የሚያግዛቸው ስልጠና መሆኑን በዕለቱ ስልጠናውን የሰጡት የሆስፒታሉ የሰው ሃብት አስተዳደር ቡድን መሪ አቶ ተስፋዬ ደንድር ገልፀዋል፡፡

የጥበቃ ሰራተኞች የሚጠበቅባቸውን ስራ ሁሉ በመስራት እና የተቋሙ ንብረት እና የሰራተኛውን ደህንነት በመጠበቅ በኩል ሃላፊነታቸው መወጣት እንደሚጠበቅባቸው በስልጠናው ተጠቅሷል፡፡ ሌላው ወደ ተቋሙ የሚገቡ ንብረቶች እንዲሁም ከተቋሙ የሚወጡ ማንኛውም አይነት ንብረት እና የተለያዩ እቃዎችን መቆጣጠርና የተቋሙን ንብረት በመለየት ልዩ ቁጥጥር ማድረግ እንደሚገባም ተጠቁሟል፡፡

Search articles

Recent articles

    Loading...