ስለ ስኳር ህመም ህክምና  የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና

By Sahle relation

ስለ ስኳር ህመም ህክምና  የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና

መጋቢት 29/2018 ዓ.ም

ሆስፒታላችን ከኢትዮጵያ የስኳር ህመም ማህበር ጋር በመተባበር ላለፈው 1 አመት በሆስፒታሉ ስር ክትትል ለሚያደርጉ እድሜአቸው ከ25 አመት በታች ለሆኑ የስኳር ህመም ታካሚዎች ነፃ የስኳር መለኪያ ማሽን፣ መድሃኒት (Insulin) እና መርፌ ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ አሁንም ሆስፒታሉ የተሻለ የተባለውን መድሃኒት (Analog insulin) ከዚሁ ድርጅት በማግኘቱ ስለመድሃኒቱ አጠቃቀም፣ የጎንዮሽ ጉዳት እና የመድሃኒቱ አቀማመጥ አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ሰጠ፡፡

ስልጠናው ነርስ ፣ሚድዋይፍሪ እና ፋርማሲ ባለሙያዎችን ያካተተ ነበር፡፡በቀጣይም ለሲኒየር ሃኪሞች፣ ለሜዲካል ሪዚደንት ሃኪሞች እና ለሜዲካል ኢንተርን ተማሪዎች እንደሚሰጥ ተገለፀ፡፡

በመቀጠልም በሆስፒታሉ አቅራቢያ ለሚገኙ እድሜያቸው ከ25 አመት በታች ለሆኑ የስኳር ህመም ታካሚዎች ይህንን እድል መጠቀም እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

Search articles

Recent articles

    Loading...