በሆስፒታላችን የመጀመሪያ የሆነው የግማሽ ዳሌ መገጣጠሚያ ቅየራ

By Sahle relation

በሆስፒታላችን የመጀመሪያ የሆነው የግማሽ ዳሌ መገጣጠሚያ ቅየራ

የምስራች ለህክምና አገልግሎት ፈላጊ ማህበረሰባችን በሙሉ ወሳኝ ስኬት በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል!!

በሆስፒታላችን የመጀመሪያ የሆነው የግማሽ ዳሌ መገጣጠሚያ ቅየራ ተጀመረ፡፡

በመውደቅና በተለያየ አደጋ ምክንያት የታፋ እጥንት እና አንገት ስብራት የገጠማቸው ታካሚዎች ይህን የህክምና አገልግሎት ለማግኘት ወደ አዲስ አበባ በመሄድ ብዙ እንግልት እና ስቃይ ይደርስባቸው እንደነበር በሆስፒታሉ የአጥንት እና የመገጣጠሚያ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ሃኪም ዶክተር አብርሃም ገብሬ ገለፁ፡፡

በቀጣይነትም አገልግሎት ለሚፈልጉ ታካሚዎች ይህን የዳሌ ቅየራ ህክምና አገልግሎት በሆስፒታላችን የሚሰጥ መሆኑን ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነው፡፡

Search articles

Recent articles

    Loading...