በኢንዶስኮፒ ማሽን የሚሰጥ የምርመራ እና የህክምና አገልግሎት
By Sahle relation
በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በኢንዶስኮፒ ማሽን የሚሰጥ የምርመራ እና የህክምና አገልግሎት፡፡
ከሳምንታት በፊት የኢንዶስኮፒ ምንነት እና አገልግሎት በተመለከተ ግንዛቤ መስጠታችን ይታወቃል፤ኢንዶስኮፒ(Endoscopy) ማሽን ማለት ቀጭን ተጣጣፊ ጫፉ ላይ ካሜራ እና መብራት ያለው ጉሮሮ፣ጨጓራ እና የላይኛው የአንጀት ክፍል ላይ ምርመራና ህክምና ለመስጠት የሚያገለግል የህክምና ማሽን ነው፡፡
በሆስፒታሉ የሚሰጡ የኢንዶስኮፒ (Endoscopy) ማሽን የምርመራ እና የህክምና አገልግሎቶች፡-
1) ምግብም ሆነ ፈሳሽ ነገሮችን በምንውጥበት ጊዜ ጉሮሮአችን ላይ ህመም ወይም መዋጥ መቸገር ካለ
2) የጨጓራ አሲድ ወይም ጉሮሮ የመመለስ ችግር (GERO)ምልክት ካለ
3) የጉሮሮ፣ጨጓራ እና የላይኛው የአንጀት ክፍል ቁጣ ወይም ቁስለት ሲፈጠር
4) የጉሮሮ፣ጨጓራ እና የላይኛው የአንጀት ክፍል ዕባጭ ወይም ካንሰር ሲኖር ለመመርመርና ናሙና ለመውሰድ
5) የጨጓራ ህመም ምልክት ላለበትና ክብደት መቀነስ ሲኖር
6) መንስኤው ያልታወቀ የደም ማነስ ሲፈጠር
7) ማንኛውም ዕድሜው ከ50 ዓመት በላይ የሆነና የጨጓራ ህመም ስሜት ሲኖር
8) ከጨጓራ እና ከላይኛው የአንጅት ክፍል መድማት ሲኖር ማስቆምና ችግሩን ለይቶ ማወቅ
9) የጉበት ህመም ላለባቸው ሰዎች portal hypetention እና የመሳሰሉትን የበሽታ አይነቶችን ፣መመርመር፣መለየትና የህክምና አገልግሎት እንደሚሰጥ በሆስፒታሉ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ሃኪም እና በኢንዶስኮፒ ማሽን ስልጠናውን ወስደው የምርመራ እና የህክምና አገልግሎት ላይ ባለሙያ የሆኑት ዶክተር ይርጋለም ሀይሉ ገልፀዋል፡፡