ነርቭ መልዕክት ከተለያዩ የሰውነታችን ክፍሎች ወደ አንጎልና ህብረ ሰረሰር የሚያመላልስ የሰውነታችን የኤሌክትሪክ ሽቦ ነዉ
By Sahle relation

ለጥንቃቄዎ
የነርቭ በሽታ/
ነርቭ መልዕክት ከተለያዩ የሰውነታችን ክፍሎች ወደ አንጎልና ህብረ ሰረሰር የሚያመላልስ የሰውነታችን የኤሌክትሪክ ሽቦ ነዉ ።
በሰውነታችን ሦስት ዋና ዋና የነርቭ ዓይነቶች ሲኖሩ እነዚህም የሰሜት/sensory, የሞተርና የአውቶኖሚክ/ከኛ ቁጥጥር ውጪ ያሉ ነርቮች ናቸው ።
የስሜት ነርቮች / Sensory nerves ፡ የህመም ፡የሙቀት አንዲሁም የአቅጣጫና ሚዛን/position and balance መልዕክት ወደ አንጎል ያስተላልፋሉ።እነዚህ ነርቮች ሲታመሙ እነደ መርፌ የሚዋጋ ሕመም ፣የማቃጠል ስሜት ፣የመደንዘዝ ስሜት ፣በሰውነት ውስጥ እንደ ትል የመሄድ ስሜትና ያላበጠ የሰውነት ክፍል ያበጠ መምሰል ። ባላንስ ማጣት ፣የጆሮ መጮህና ማዞርም ሊያጋጥም ይችላል ።
የሞተር ነርቮች /Motor nerves:እነዚህ ነርቮች ጡንቻንና እጢውችን የሚያዙ ሲሆን በበሽታ በሚጠቁበት ጊዜ የጡንቻ መዛል ፣የሰውነት አካል መስነፍ፣ከወንበር መነሳት ማስቸገር ሊያጋጥም ይችላል።
የአውቶኖሚክ ነርቮች /autonomic nerves ፡ እነዚህ ነርቮች እኛ ማናስተውላቸው የሰውነታችን የውስጥ ስራዎችን ይቆጣጠራሉ። የልብ ምታችንን ፣የአንጀታችን ፣የሳንባችንን ስራዎችን እኛ ሳናውቅ ይቆጣጠራሉ ።አነዚህ ነርቮች ሲጎዱ ስንቆም ማዞርና ብዥብዥ ማለት፣የአፍ መድረቅ ፣የሽንት ማስቸገር ፣የሆድ ድርቀት ፣ስንፈተ ወሲብ ሊያጋጥም ይችላል
አንድ ሰው ከላይ የተዘረዘሩት ሁሉም ባንድ ላይ ወይ ደሞ በተናጠል ሊያጋጥሙት ይችላሉ ። አንድ ነርቭ ብቻ ሊጠቃም ይችላል ። ለምሳሌ አንድ እጅ ብቻ በሚድያን ነርቭ ሕመም ምክንያት ሊታመም ይችላል ።ይህ ካርፓል ተነል ሲንድረም /carpal tunnel syndrome ይባላል ።ሌላ ሰው ደሞ ብዙ ነርቮች ባንዴ ሊታመም ይችላል።ሁለቱም እጆች፣ሁለቱም እግሮቹ ሊያሙት ይችላል።
ምክንያቶች
1.የስጋ ደዌ በሽታ ፣ይህ ባደጉ ሀገሮች ያልተለመደ ክስተት ቢሆንም በሀገራችን ግን በብዛት ይገኛል።ይህ በሽታ ነርቮችን በማጥቃት ይታወቃል።
2. የስኳር በሽታ ፣ግማሽ ያህሉ በስኳር በሽታ የተያዙ ሰዎች የነርቭ ህመም የሆነ ሰዓት ላይ ይገጥማቸዋል። በተለይ ስኳራቸው ለረጅም ጊዜ ከፍ ብሎ ከቆየ ይህ ችግር ይገጥማቸዋል። ይህን ሳይከሰት መከላከል እንጂ ከተከሰተ በዃላ ማዳን ስለማይቻል ስኳር ያለባቸው ሰዎች ስኳራቸዉን መቆጣጠር አለባቸው ።
3.የቫይታሚን እጥረት:የቫይታሚን B12፣ ቫይታሚን D እጥረት ሲኖር ነርቭ በሽታ ይከሰታል ።ይህም የተመጣጠነ ምግብና ቫይታሚን በመውሰድ ይስተካከላል።
4. ኢንፌክሽኖች: የተለያዩ ቫይረሶች። HIV, Hepatitis b,c, የመሳሰሉት ።
5. የውስጥ ቁስለት/Inflammation
6. የታይሮክሲን ሆርሞን እጥረት
ከላይ የዘረዘርናቸው ዋናዎቹ ሲሆኑ ከመቶ በላይ የሆኑ ሌሎች ምክንያቶች አሉ። ለአንድ ሶስተኛው ታማሚ ግን ሙሉ ምርመራ ቢደረግም እስካሁን ባለው የህክምና እውቀት ምክንያቱ አይታወቅም ።
የሚያስፈልጉ ምርመራዎች
1.ሙሉ የሰውነት ምርመራ በሰለጠነ ሐኪም
2. የስኳር ፣የ ኤችአይቪ እና ሌሎች ከላይ መንሴ ይሆናሉ ተብለው የተጠረጠሩ በሽታዎች ምርመራ
3. የነርቭ ምርመራ /electromyography and nerve conduction study
4. MRI እና ሌሎችም እንደ በሽታው ሁኔታ
የህክምና አማራጮች
1.እግርን ወይም እጅን ህመሙ በተነሳ ሰዓት በቀዝቃዛ ውሃ ለአስር ደቂቃ መዘፍዘፍ ።
ይህ በቤት ውስጥ ሊሰራ የሚችል ቀላሉ ዘዴ ሲሆን ለብዙ ቀላል ህመም ላላቸው ሰዎች ይሰራል ።
2.ፓራስታሞል/አይቡፕሮፌን መውሰድ:ይህንንም በቤት ውስጥ ለቀላል ህመም መውሰድ ይቻላል፡፡
ምንጭ፡ ደቡብ ክልል ጤና ቢሮ