የፋርማሲ አገልግሎት
By Sahle relation
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለማህበረሰቡ ዘርፈ ብዙ የህክምና አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል፡፡
በሆስፒታሉ ከሚሰጡ አገልግሎቶች መካከልም የፋርማሲ አገልግሎት አንዱ ሲሆን ሆስፒታሉ የተገልጋይን እርካታ ለማሳደግ ሲል ተጨማሪ መድሃኒት ቤት ከፍቶ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ጥቂት አመታትን አስቆጥሯል፡፡ ታዲያ ይህ የማህበረሰብ መድሃኒት ቤት የማህበረሰቡን የኢኮኖሚ አቅምን ያገናዘበ በመሆኑ ትልቅ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ተባለ፡፡ መድሃኒት ቤቱ እንደሚታወቀው በጉብርየ ክፍለ ከተማ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን አጠገብ የዩኒቨርሲቲ መምህራን መኖሪያ አፓርትመንት ውስጥ ሲሆን መድሃኒት ቤቱ የማህበረሰቡ ፍላጎት ለማሟላት በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡ይሁን እንጂ ሙሉ በሙሉ የማህበረሰቡን ፍላጎት ለማሟላት የመድሃኒት አቅርቦት ላይ ተግዳሮቶች እንዳሉ በማህበረሰብ መድሃኒት ቤት የፋርማሲ ባለሙያ እና አስተባባሪ አቶ ፋንቱ ግርማ ገልፀዋል፡፡ሆስፒታሉ የመድሃኒት አቅርቦት(የግዢ ስርዓት) የሚያደርገው መመሪያና ደንብን ጠብቆ በኦን ላየን (On line) ከመድሃኒት አቅራቢ ድርጅት በመሆኑ የተፈለጉ መድሃኒቶች በጊዜው አለመቅረባቸው ትልቅ ተግዳሮት እንደፈጠረባቸውም አቶ ፋንቱ ጠቁመዋል፡፡ ሌላው ለማህበረሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት ያስችል ዘንድ ከሆስፒታሉ መድሃኒት ቤት ጋር በመናበብ ማህበረሰቡ በቀላሉ መድሃኒት ማግኘት እንዲችል የማመቻቸት ስራ በቅንጅት እየተሰራ እንዳለ የፋርማሲ ባለሙያ አቶ አወቀ አለማየሁ ተናግረዋል፡፡
የማህበረሰብ መድሃኒት ቤት ከዚህም በላይ ትኩረት ተሰጥቶት ከተሰራ ለማህበረሰቡ ትልቅ ጠቀሜታ ሊሰጥ እንደሚችልም ተገልፆአል፡፡